በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የአባት እናት አምላክ አምልኮ እምነት ተቋም አማኞች እነደ ባህላ ቸው አና እሴታቸው ሃገራዊ በሆነ ልማድ ከአንድ ፈጣሪ በመንፈስ የሚገናኙበትና ሀይማኖትን ዘርን ቋነቋን ሳይለይ በአንድነት ተሰብስበው አንዱን አምላክ የሚያመለኩበት የጥንት የጠኋት ቀደምት እምነት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የአባት እናት አምላክ አምልኮ እምነት ተቋም አማኞች እነደ ባህላ ቸው አና እሴታቸው ሃገራዊ በሆነ ልማድ ከአንድ ፈጣሪ በመንፈስ የሚገናኙበትና ሀይማኖትን ዘርን ቋነቋን ሳይለይ በአንድነት ተሰብስበው አንዱን አምላክ የሚያመለኩበት የጥንት የጠኋት ቀደምት እምነት ነው፡፡
በኢትዮጰያ ሀገር በቀል የአባት እናት አምላክ አምልኮ እምነት ተቋም የአምልኮ ስርዓት ዋና ዋና ባህሪያትና ባህላዊ ገፅታዎች
በኢትዮጵ ያ ሀገር በቀል የአባት እናት አምላክ አምልኮ እምነት ተቋም በኢትዮጵያ ውስጥ ከተለመዱ ሀገር በቀል እምነቶች ውስጥ ከውቃቢ /ጠባቂ መንፈስ ቅዱስ/ ጋር በተያያዘ መልኩ በኢትዮጵያ ባህል ልማድ ጋር የተቆራኘ እና ሲወርድ ሲወራረድ የመጣ የአምልኮ ስርአት ነው፡፡ የዚህ እምነት ስርዓት በጹህፍ ከተደገፉ ሐይማኖቶች ይልቅ በቃል በልማድና በህገ ልቦና በተግባር ከእናት አባት ወደ ልጅ ሲወራረድ የመጣ አምልኮ ስርዓት ነው፡፡ በእምነቱ ሰላም ማውረድ የተጣሉትን ማስታረቅ እውነትን መፈለግ ትልቅ ቦታ የሰጣቸዋል፡፡ ቡና ማፍላቱ ጨፌ መጎዝጎዙ አጣን መጨሱና የመስአዋት አቀራረቡ የእንስሳት አርድ ስርአቱና የገበታ ስነ-ስርአቱ ከኢትዮጵያን ባህል ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከነበረው የገዳ ስርአት ውስጥ ከሚመዘዘው የዋቄ ፈና ሀይማኖት ጋር ተመሳሳይነት ያለው በቻ ሳየሆን ለብዙ ዘመናት አንድ መስሎ ተመሳስሎም የኖረበት ጊዜ ቀላል አይደለም፡፡ የአባት እናት አምላክ አምልኮ የሰው ልጆችን ከአነዱ አምላክ ጋር በመንፈስ የሚያገናኝ ተፈጥሮአዊ የሆነ የአምልኮ ስርኣት ነው፡፡ አምነቱ ገልጽ ስርዓት ያለው እና በጥንታዊ ሃገር በቀል መንፈሳዊ አውቀት ላይ የተኮረ ሆኖ ሰዎችን በዘር በቋንቋ ወይም ሃይማኖት ሳይለይ በአንድነት የሚያስተሳስር ከፈጣሪና ከተፈጥሮ ጋር በሰላም ለመኖር የሚያስችል ጥበብን የያዘ ለመሆኑ አምሰቱመሰረታዊ አእማዶች በግልጽ ያስረዳሉ፡፡
የአምሰቱ መሰረተ ሃሳቦች ማጠቃለያ
1. አግዚያብሄር (GOD) ሰማይን ምድርን እንዲሁም በነሱ ውሰጥ ያለውን ፍጥረት የፈጠረ የሃያላን ሁሉ አምላክ --አንድ አምላክ
2. ውቃቢ አምላክ ከራሱ ከእግዚያብሄር መንፈሳዊ ባህር የተጨለፉ የእግዚያብሄርን ክብር የሚያስጠብቁና የሰውን ልጅ የሚያገልግሉ የሚጠብቁ በመንፈስ ቀዱስ የተቃኙ ናቸው፡፡
3. በለውቃቢ ፤( ውቃቢ አምላክ ያደረበት)ለፍጥረታት ሁሉ እኩል የሚፈርድ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ ያደርጋል ከሃጢያተኞች ከሟርተኞች እጅ ያሰጥላል
· የባለውቃቢወች ሚና እግዚያብሄር ሰውን እንዲያገለግሉ መንፈሱን የሰጣቸው ባለውቃቢዎች እንደ አማለጅ(መካከለኛ)በመሆን ያገለግላሉ
· የሰው ልጅበነዚህ በለውቃቢወች አማካኝት ህመሙን ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ችግሩን የሚፈታባቸው የእምነቱ መሪዎች ናቸው፡፡
4. ፅድቅን መጠበቅ፤ በሙሉ ህይወትን በእግዚያብሄር ቅዱስ መንፈስ ምሪትና አዛኝነት መምራት
5. ከሃጢያት መጠበቅ፤እግዚያብሄር የፈጠረውን ህይወት ያለው ፍጥረትን ሁሉ ማክበር መንከባከብ እና ከክፉ ነገር ሁሉ መቆጠብ
የአባት እናት አምላክ አምለኮ/የውቃቢ እምነት / ማንነት ባህረይ ከሌሎች ሀይማኖቶች ወይም የባህል ስርአቶች (እንደ ዋቄፈና ኦርቶዶክስ እስልምና) ጋር ያለው ተዛምዶና የሚከተላቸው ትምህርቶች
1. ከዋቄፈታ አና ከገዳ ስርዐት ጋር ያለው ተዛምዶ
· ተመሳሳይነት ፤ የአባት እናት አምላክ አምለኮ ከአንድ አምላክ አምለኮ(monotheism) አንጻር ከክርስቶስ ልደት በፊት ከነበረው የገዳ ስርዓት እና ከዋቄ ፈና እምነት ጋር አምልኮታዊ አፈጻጸሙ ተመሳሳይነት አለው
· ልዩነት፤ ዋቄፈታ ራሱን የቻለ የኦሮሞ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ስርአት ሲሆን የአባት እናት አምላክ እምነት የአምለኮ ስርአት በወቄፈታ እምነት ውሰጥ አነደ ዋና የእምነቱ አካል ተደርጎ ይከናወናል፡፡ ነገር ግን ዋቄፈታ አብዛኛውን ጊዜ የአሮሞ ማህበረሰብን ሴራ (ህግ) ባህል ብቻ የሚከተል ስረአት ሲሆን የአባት እናት አምላክ አምልኮ ብሄርን ጎሳን ቋነቋን ሃይማኖትን ሳይለይ ወቄፈታውም እስላሙም ክርስቲያኑም ከአንዱ አምላክ በመንፈስ የሚገናኙበት አምለኮ ስርአት ነው
· በእስልምናና በክርስትና አመለካከት አንድ አንድ የእምነቱ አባቶች ሆነ ብለው በሚሰብኩት አሉታዊ አሰተምህሮ ምክኒያት የአባት እናት አምላክ አምልኮ አማኞች በመሳቀቅ በየቤታቸው በሚስጥር እምነታቸውን እንዲቀጥሉ ወይም ከእምነቱ አንዲወጡ ተገደዋል፡፡
2. የመንፈስ መመሪያ እና የጽሁፎች አጠቃቀም
· የእለት ተእለት መመሪያ የእምነቱ ተከታዮች ተእት እለት ለሚያጋጥማቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መነፈሳዊ ችግሮች በህገ ልቦና በቃልና በመንፈስ አየተመራ መፍትሄ የሰጣል
· የቅዱሳን መፃህፍት አጠቃቀም ምንም እንኳን በህገ ልቦና በቃልና በመንፈስ የሚመራ ቢሆንም ጥንታዊ መፃህፍትን ለታሪክ ለትምህርትና ለማስረጃነት ይቀበላል፡፡ እነደብሉይኪዳን አዲስ ኪዳን ቁራአንን የመሳሰሉትን በእውነትና በመንፈስ በመመርመር ለማስረጃነት ሊጠቀም ይችላል፡፡
A place of faith
A place of faith